​ዐፄዎቹ ከመስመር ተከላካዩ ጋር በስምምነት ተለያይተዋል

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

ፋሲል ከነማ የአስራ ዘጠኝ ወር ኮንትራት ከሚቀረው ተጫዋቹ ጋር መለያየቱን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች፡፡

በኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የ2013 የውድድር ዘመን ሻምፒዮን መሆን የቻለውን ፋሲል ከነማን በክረምቱ የዝውውር መስኮት ከተቀላቀሉ ተጫዋቾች መካከል የግራ እና የቀኝ መስመር ተከላካዩ አብዱልከሪም መሐመድ አንዱ ነው፡፡ የቀድሞው የደቡብ ፓሊስ ፣ ሀዋሳ ከተማ ፣ ሲዳማ ቡና ፣ ኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋች የነበረው አብዱልከሪም ፈረሰኞቹን በመልቀቅ በነሀሴ ወር ለሁለት ዓመት ለዐፄዎቹ ለመጫወት ፊርማውን አኑሮ ያለፉትን ስድስት ወራት ቆይታ የነበረው ቢሆንም ከክለቡ ጋር ቀሪ የአስራ ዘጠኝ ወራት  ውል እየቀረው በስምምነት መለያየቱን ተጫዋቹ ለሶከር ኢትዮጵያ አሳውቋል፡፡

ተጫዋቹ “መጫወት የሚያስችል አቅም እያለኝ በተጠባባቂ ወንበር ለመቀመጥ አልመጣውም” በማለት ከወር በፊት የልቀቁኝ ደብዳቤ አስገብቶ መልቀቂያውም ተቀባይነት አግኝቶ በስምምነት ለመለያየቱን ገልጿል፡፡ በክለቡ በኩል ባገኘነው መረጃ ደግሞ ተጫዋቹ በሚሰለፍበት ቦታ የተሻለ ብቃት ያላቸው ተጫዋቾች ስላሉ የመሰለፍ ዕድል አለማግኘቱ ምቾት እንዳልሰጠው በመጥቀስ ራሱን በተሻለ ለማሳየት ወደሌላ ክለብ ሄዶ መጫወትን በመምረጥ ያስገባውን የልቀቁኝ ደብዳቤ በመቀበል መለያየቱ እንደመጣ ይጠቁማል። ተጫዋቹ በአሁኑ ሰዓትም የክለቡን ካምፕ በመልቀቅ ወደ ሚኖርበት ሀዋሳ ማምራቱን አውቀናል።