ቡናማዎቹ በዝውውሩ መሳተፍ ጀምረዋል

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

በዛሬው ዕለት በተከፈተው የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ኢትዮጵያ ቡና የመጀመሪያ ተጫዋች አስፈርሟል።

በአሠልጣኝ ካሣዬ አራጌ የሚመራው ኢትዮጵያ ቡና በዘንድሮ የውድድር ዓመት 20 ነጥቦችን በመያዝ በደረጃ ሰንጠረዡ አካፋይ ቦታ ላይ እንደተቀመጠ ይታወቃል። ዓምና በሊጉ ብዙ ግቦችን ሲያስቆጥር የምናውቀው ቡድኑም ዘንድሮ ፊት መስመር ላይ መሳሳቱን ተከትሎ ዛሬ በተከፈተው የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ላይ በመሳተፍ አጥቂ አስፈርሟል። በዚህም በውድድር ዓመቱ መጀመሪያ ለገላን ከተማ ፈርሞ የነበረው ተመስገን ገብረኪዳን ቡናማዎቹን ተቀላቅሏል።

2010 ከጅማ አባ ጅፋር ጋር የፕሪምየር ሊግ ዋንጫን እንዲሁም 2011 ላይ ከመከላከያ ጋር የጥሎ ማለፍ እና የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫን (መስከረም ላይ የተደረገው የ2010 ውድድር) ያገኘው ተጫዋቹም ለቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት የሚያቆጠውን ውል መፈረሙን ክለቡ በማኅበራዊ ገፁ ይፋ አድርጓል።