ሲዳማ ቡና የግራ መስመር ተከላካዩን ውል አራዝሟል

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

ሲዳማ ቡናን ባሳለፍነው ዓመት አጋማሽ የተቀላቀለው እና ውሉ የተገባደደው የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹ ለተጨማሪ ዓመት በክለቡ ውሉ ታድሶለታል፡፡

የ2014 የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ አጀማመሩ ያላመረው እና የአንደኛውን ዙር የመጨረሻ ሳምንታት ጨዋታዎቹን በማሳመር ወደ ዋንጫ ፉክክሩ የተጠጋው ሲዳማ ቡና ዙሩን ካደረጋቸው 15 ጨዋታዎች በሰበሰበው 25 ነጥብ 5ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡ ለሁለተኛው ዙር ውድድር አዳዲስ ተጫዋቾች እና ውላቸውን የተጠናቀቁ ተጫዋቾችን ውል እንደሚያራዝም የሚጠበቀው ሲዳማ ቡና የግራ መስመር ተከላካዩን መሐሪ መናን ውል ለአንድ Xaመት ከስድስት ወራት ስለ ማራዘሙ ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች፡፡

የእግር ኳስ ህይወቱን ከሀዋሳ ከጀመረ በኋላ ለሲዳማ ቡና ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እንዲሁም ባሳለፍነው ዓመት አጋማሽ በድጋሚ ወደ ቀድሞው ክለቡ ሲዳማ ቡና ተመልሶ መልካም የውድድር ጊዜን በማሳለፍ ላይ የሚገኘው ተጫዋቹ በክለቡ ባሳየው ጥሩ የውድድር ጊዜ መነሻነት ለተጨማሪ ዓመት በክለቡ ለመቆየት ፊርማውን አኑሯል፡፡

ከዝውውር ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የዝውውር መስኮት ዛሬ እንደተከፈተ የሚታወቅ ሲሆን ሶከር ኢትዮጵያም እንደተለመደው ወቅታዊ መረጃዎችን ወደ እናንተ የምታደርስ ይሆናል።