​ሰበታ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈርሟል

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

ያለፉትን ሳምንታት ከቡድኑ ጋር ልምምድ ሲሰራ የከረመው ጋናዊ ተጫዋች በይፋ ለሰበታ ከተማ ፊርማውን አኑሯል።

ከትናንት በስትያ በተጠናቀቀው የመጀመሪያው ዙር የሊጉ ውድድር ደካማ ብቃት በማሳየት በደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ የተቀመጠው ሰበታ ከተማ መጋቢት 19 ለሚጀምረው የሁለተኛ ዙር ውድድር ራሱን በአዳዲስ ተጫዋቾች እያጠናከረ ይገኛል። ከቀናት በፊት ዩጋንዳዊውን አጥቂ ዴሪክ ንስባምቢ አስፈርሞ የነበረው ክለቡ የዝውውር መስኮቱ እስኪከፈት ድረስ በስብስቡ ቀላቅሎ ልምምድ ሲያሰራው የነበረውን ቢስማርክ አፒያን ከደቂቃዎች በፊት በይፋ አስፈርሟል።

2010 ላይ ጅማ አባ ጅፋርን በመቀላቀል የኢትዮጵያን እግር ኳስ የተዋወቀው አፒያ ከዛም ወደ ስሑል ሽረ እና ሀዲያ ሆሳዕና አምርቶ የእግር ኳስ ህይወቱን ቀጥሏል። ዓምና ከክፍያ ጋር በተያያዘ ከከቤራዎቹ ጋር ውሉ ሳያልቅ የተለያየው የመሐል እንዲሁም የመስመር አጥቂው ከወራት በኋላ ደግም ወደ ሀገራችን በመመለስ ለሰበታ ከተማ የአንድ ዓመት ውል በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ተገኝቶ መፈረሙን አረጋግጠናል።