የከፍተኛ ሊግ የምድብ ለ 13ኛ ሳምንት ሁለተኛ ቀን ውሎ

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

በባቱ ሼር ሜዳ እየተካሄደ የሚገኘው የምድብ ለ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 13ኛ ሳምንት ዛሬ በሁለት ጨዋታዎች ሲገባደድ ለገጣፎ ለገዳዲ እና ስልጤ ወራቤ በሰፊ ግብ ተጋጣሚዎቻችውን አሸንፈዋል።

8፡00 ላይ የዕለቱ ተጠባቂ ጨዋታ በቡታጅራ እና ለገጣፎ መካከል ተከናውኗል። በምድቡ ፉከክር ላይ የሚገኙትን ቡድኖች ያገናኘው ጨዋታ በለገጣፎ 4-0 አሸናፊነት ተጠናቋል። ልደቱ ለማ በ9ኛው 24ኛው እና 84ኛው ደቂቃዎች ሦስት ጎሎችን አስቆጥሮ ሀትትሪክ ሲሰራ ፋሲል አስማማው በ74ኛው ደቂቃ ሌላኛውን ጎል ማስቆጠር ችሏል።

ድሉን ተከትሎ ለገጣፎ ለገዳዲ ነጥቡን 25 በማድረስ ከፍተኛ ፉክክር እየተደረገበት በሚገኘው ምድብ ለ ከመሪው ቡራዩ ጋር በነጥብ ተስተካከሎ በግብ ልዩነት በመበለጥ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

የሳምንቱ የመጨረሻ ጨዋታ በካፋ ቡና እና ስልጤ ወራቤ መካከል ተከናውኖ ስልጤ ወራቤ 3-0 አሸንፏል። የስልጤ ወራቤን የድል ግቦች አቤኔዘር ኦቴ በ4ኛው፣ ፀጋአብ ዮሴፍ በ70ኛው እንዲሁም ሳዲቅ ሴቾ በ73ኛው ደቂቃ ላይ ማስቆጠር ችለዋል።

በውጤቱ መሰረት ስልጤ ወራቤ ነጥቡን 17 በማድረስ በሰንጠረዡ ወገብ ላይ ሲቀመጥ ካፋ ቡና በ14 ነጥብ 8ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።