​ኢትዮጵያን የሚገጥመው የጋና ብሔራዊ ቡድን ጉዞ ጀምሯል

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]
ከነገ በስትያ ከኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ጋር የሚፋለመው የጋና ብሔራዊ ቡድን አመሻሽ ላይ አዲስ አበባ ይደርሳል።

በኮስታሪካ አስተናጋጅነት በሚከናወነው የሴቶች ከ20 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ ውድድር ላይ ለመሳተፍ የአህጉራችን ብሔራዊ ቡድኖች የማጣሪያ ጨዋታዎችን እያደረጉ ይገኛል። የመጨረሻው ምዕራፍ የማጣሪያ ጨዋታዎች በሳምንቱ መጨረሻ ሲጀምሩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም ከጋና አቻው ጋር የፊታችን እሁድ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይጫወታል። 

በአሠልጣኝ ቤን ፎኩ የሚመራው የጋና ሴቶች ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከተጋጣሚው ኢትዮጵያ በፊት ዝግጅቱን ጀምሮ ሲለማመድ የነበረ ሲሆን የመጀመሪያ ጨዋታውንም ለማድረግ በአሁኑ ሰዓት ጉዞ ጀምሯል። የጥቋቁር ልዕልቶቹ ዋና አሠልጣኝ ፎኩ ኢትዮጵያን ለመግጠም ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ 22 ተጫዋቾችን (3 ግብ ጠባቂዎች፣ 7 ተከላካዮች፣ 5 አማካዮች 4 የመስመር ተጫዋቾች እና 3 አጥቂዎች) እንደያዙ የሀገሪቱ ተነባቢ ድረ-ገፅ ፉቲ-ጋና ዘግቧል።

በአስገራሚ ሁኔታ ቡድኑ ውስጥ የነበሩት እና ከሀገር ውጪ በኖርዌይ የሚጫወቱት አምበሏ ኢቪሊን ባዱ እና ተከላካዩዋ ሱሳን አማ ዱሀ ባልተገለፀ ምክንያት በስብስቡ ውስጥ እንደሌሉም ታውቋል።