በዚህ ሳምንት በሚኖሩ ጨዋታዎች ዙርያ ምን ተባለ ?

የሁለተኛው ዙር የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የነገው ሲጀምር የሰዓት ለውጥ ሊደርግባቸው ይችላል ተብለው ሲነገሩ በነበሩ የዚህ ሳምንት ጨዋታዎች ዙርያ ምን ተባለ?

ከ16ኛ እስከ 21ኛ ሳምንት ድረስ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም ከነገ ጀምሮ ውድድሮች እንደሚካሄዱበት ይታወቃል። አስቀድሞ በወጣው መርሐግብር መሠረት ዘጠኝ ሰዓት እንዲሁም ምሽት አስራ ሁለት ሰዓት ጨዋታቸውን እንዲያደርጉ ፕሮግራም መውጣቱ ይታወቃል።

ሆኖም ግን የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም የፓውዛው መብራት ተከላን ለማጠናቀቅ ጥረት እየተደረገ ሲሆን አሁን ባለው ሁኔታ ተጠናቆ ለነገው ጨዋታ የሚደርስ መሆኑን በመታመኑ የሰዓት ለውጥ እንደማይኖር እና አስቀድሞ በወጣለት መርሀግብር እንደሚቀጥል ሊግ ካምፓኒው ለሶከር ኢትዮጵያ አሳውቋል።