ኢትዮጵያ ቡና ከተከላካዩ ጋር ተለያይቷል

በክረምቱ ኢትዮጵያ ቡናን ተቀላቅሎ የነበረው የመሀል ተከላካዩ በስምምነት ከክለቡ ጋር ተለያይተዋል፡፡

‌‌

በአሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ በያዝነው የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር ግልጋሎት ለመስጠት ኢትዮጵያ ቡናን ከተቀላቀሉ ተጫዋቾች መካከል አንዱ የመሀል ተከላካዩ ነስረዲን ኃይሉ አንዱ ነው፡፡ በሦስት አመት ውል ቡናማዎቹን ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ተቀላቅሎ የነበረው የቀድሞው የመከላከያ ተጫዋች በጉዳት ምክንያት አንድም ጨዋታ ለክለቡ አገልግሎት መስጠት አለመቼሉን ተከትሎ በጋራ ስምምነት ዛሬ ከክለቡ ጋር መለያየቱን ኢትዮጵያ ቡና ይፋ አድርጓል