ኤልያስ ማሞ አዲሱ ክለቡን ዳግም ተቀላቅሏል

በውድድር ዓመቱ አጋማሽ በተከፈተው የዝውውር መስኮት ወደ አዲስ ክለብ አምርቶ የነበረው እና በተለያዩ ምክንያቶች ከክለቡ ተለይቶ የነበረው አማካይ በመጨረሻም ክለቡን ተቀላቅሏል።

ኤሊያስ ማሞ ከወራት በፊት በአዳማ ከተማ የነበረው ቆይታ መጠናቀቁን ተከትሎ በአሰልጣኝ ደምሰው ፍቃዱ ወደ ሚመራው አዲስ አበባ ከተማ ዝውውሩን ማጠናቀቁን ዘግበን ነበር። ሆኖም ከህክምና እና ተያያዥ ጉዳዮች ጋር ተያይዞ ዝውውሩ ዕክል አጋጥሞት እንደነበረም አስነብበት ነበር። አሁን ባገኘነው መረጃ ግን በተጫዋቹ እና በክለቡ መካከል መተማመን ላይ በመደረሱ በዛሬው ዕለት ኤልያስ ማሞ ዳግም ቡድኑንን በመቀላቀል የመጀመርያ ልምምዱን መስራቱን አውቀናል።

ይህን ተከትሎም በቀጣይ አዲስ አበባ ከተማ በሚኖረው የሊጉ ጨዋታዎች ላይ ልምድ ያለውን አማካኝ ግልጋሎት የሚያገኝ ይሆናል።