የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰላለፍ ታውቋል

10:00 ላይ ከናይጄሪያ አቻው ጋር ወሳኝ ጨዋታ የሚጠብቀው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰላለፍ ታውቋል።

በሕንድ ለሚደረገው የሴቶች ከ17 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ የመጨረሻው የማጣሪያ ምዕራፍ ላይ የደረሰው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ዛሬ 10:00 ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ናይጄሪያን ያስተናግዳል።

አሰልጣኝ እንዳልካቸው ጫካ በዚህ የመጨረሻው የደርሶ መልስ ማጣሪያ መርሐ ግብር ቀዳሚ ጨዋታ ላይ በመጀመሪያ ተሰላፊነት የሚጠቀሟቸው ተጫዋቾች ዝርዝር በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ይፋ ሆኗል።

የብሔራዊ ቡድኑ የመጀመሪያ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል

አበባ አጄቦ

ፀሐይነሽ በቀለ
መሰረት ማሞ (አ)
ሰናይት ሸጎ
መታሰብያ ክፍሌ

ትንቢት ሳሙኤል
ቤተልሔም ግዛቸው
ትሁን አየለ

እሙሽ ዳንኤል
ቁምነገር ካሣ
እየሩስ ወንድሙ