የአዲስ አበባ ከተማ የቡድን አባላት ዝርፊያ ተፈፀመባቸው

በሲዳማ ቡና ሽንፈት ያስተናገድው የአዲስ አበባ ከተማ የቡድን አባላት ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ ዝርፊያ እንደተፈፀመባቸው ሶከር ኢትዮጵያ አውቃለች።

ረፋድ ላይ በ29ኛ ሳምንት ወሳኙን ጨዋታቸውን ከሲዳማ ቡና ጋር ያደረጉት አዲስ አበባ ከተማዎች 2-1 መሸነፋቸው ይታወሳል። ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ ወደ መልበሻ ክፍል ባመሩበት ወቅት የሰባት ተጫዋቾች የእጅ ስልክ መሰረቁን አረጋግጠናል። ብዙም ያልተለመደው ይህ ጉዳይ እንዴት ሊፈጠር ቻለ የሚለውን የባህር ዳር ከተማ ዘጠነኛ ፖሊስ ጣቢያ ጉዳዮን በመያዝ ምርመራ እያደረገ ሲሆን በድርጊቱ የተጠረጠሩ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ታውቋል።

ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ በድርጊቱ ያዘኑት የአዲስ አበባ ከተማ የቡድን አባለት ጉዳዮ በፍጥነት ተጣርቶ ምላሽ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። ሶከር ኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ ተከታትላ የምታቀርብ ይሆናል።