የጣና ሞገዶቹ የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች ወደ ቡድናቸው ቀላቅለዋል

ባህር ዳር ከተማ ወደ ዝውውሩ በመግባት ሦስተኛ ፈራሚውን አግኝቷል።

አሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ ቡድናቸውን በቀጣይ ለማጠናከር እንቅስቃሴ በማድረግ ያሬድ ባዬ እና ዱሬሳ ሹቢሳን ማስፈረማቸው ሲታወቅ አሁን ደግሞ ሦስተኛ ፈራሚያቸው አግኝተዋል።

በዚህም ለቡድኑ ፊርማውንም ያኖረው ፍፁም ጥላሁን መሆኑ ሲታወቅ ለሁለት ዓመት በጣና ሞገዶቹ የሚያቆየውን ውል ፈፅሟል።

በቅዱስ ጊዮርጊስ ታዳጊ ቡድን ተገኝቶ በኢትዮጵያ ቡና ተስፋ ቡድን የተጫወተው ፍፁም ያለፉትን ሁለት ዓመታት ከአዲስ አበባ ከተማ ጋር ጥሩ ጊዜ ማሳለፉ ይታወቃል።