ሽመክት ጉግሳ ውሉን አራዝሟል

ፋሲል ከነማ የመስመር ተጫዋቹን ውል ማራዘሙን ይፋ አድርጓል።

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ከቀናት በፊት ቢከፈትም በርካታ ክለቦች የነባር ተጫዋቾቻቸውን ውል በማደስ እና አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም ላይ ተጠምደው ይገኛሉ። እስካሁም በዝውውሩ ምንም ተሳትፎ ያላደረገው ፋሲል ከነማ ደግሞ የመስመር ተጫዋቹ ሽመክት ጉግሳን ውል ለተጨማሪ ሁለት ዓመት ማራዘሙ ታውቋል።

2011 ላይ ዐፄዎቹን ተቀላቅሎ ግልጋሎግ ሲሰጥ የነበረው ሽመክት ካቻምና ከክለቡ ጋር የሊጉን ዋንጫ ማንሳቱ አይዘነጋም።