ፌዴሬሽኑ ወልቂጤ ከተማ ላይ ውሳኔ አሳልፏል

ከአሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው እና እዮብ ማለ ጋር በተገናኘ ፌድሬሽኑ በወልቂጤ ከተማ ላይ ውሳኔን አሳልፏል፡፡

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት የወልቂጤ ከተማ አሰልጣኝ የነበሩት አሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው እና ረዳት አሰልጣኝ እዮብ ማለ ቡድኑን እየመሩ የውድድር ዓመቱን ቢጀምሩም የሊጉ የአንደኛው ዙር የመጨረሻ ጨዋታዎች ላይ ሁለቱንም አሰልጣኞች ክለቡ ከስራ ገበታቸው በማገድ በምትካቸው አዲስ አሰልጣኝ መሾሙ ይታወሳል፡፡ ሁለቱም አሰልጣኞች ለፌዴሬሽኑ የዲሲፕሊን ኮሚቴ ከስራ የታገድንበት ሁኔታ አግባብ አይደለም በማለት ቅሬታቸውን ማቅረባቸውም አይዘነጋም።

ፌድሬሽኑም ከክለቡ ጋር አሰልጣኞቹ ውላቸው ተቋርጦ የደምወዝ ክፍያቸው ይፈፀም በማለት በማለት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ በዚህም መሠረት ዋና አሰልጣኝ ለነበሩት ጳውሎስ ጌታቸው የአራት ወር ፣ ረዳት አሰልጣኝ ለነበሩት እዮብ ማለ ደግሞ የሦስት ወር ክፍያቸውን ክለቡ በሰባት ቀናት ውስጥ እንዲፈፅም ስለመወሰኑ የአሰልጣኞቹ ህጋዊ ወኪል እና የህግ ባለሙያ የሆኑት አቶ ብርሀኑ በጋሻው ነግረውናል።