አርባምንጭ ከተማ የአሰልጣኙን ውል አራዝሟል

አርባምንጭ ከተማን ከከፍተኛ ሊጉ አሳድገው በፕሪምየር ሊጉ አብረው የቀጠሉት አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ውላቸውን አድሰዋል።

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተሳትፎ እያደረገ የሚገኘው አርባምንጭ ከተማ የአሰልጣኙ መሳይ ተፈሪን ውል ማራዘማቸውን ክለቡ ለሶከር ኢትዮጵያ አሳውቋል፡፡

በአሰልጣኝነት በወላይታ ድቻ ከእግር ኳሱ ማህበረሰብ ጋር በመተዋወቅ በክለቡ መልካም ጊዜን ያሳለፉት አሰልጣኝ መሳይ በመቀጠል በፋሲል ከነማ እንዲሁም ያለፉትን አራት ዓመታት አርባምንጭን እያሰለጠኑ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ዳግም መመለስ የቻሉ ሲሆን ኮንትራታቸው መጠናቀቁን ተከትሎ አምስተኛ ዓመት ቆይታ እንዲኖራቸው በክለቡ በዛሬው ዕለት ውላቸው ታድሶላቸዋል፡፡