ቡናማዎቹ ከአማካይ ተጫዋቻቸው ጋር በስምምነት ተለያይተዋል

በዘንድሮ ዓመት ኢትዮጵያ ቡናን የተቀላቀለው አማካኝ በስምምነት መለያየቱ ተረጋግጧል።

ውል ካላቸው ተጫዋቾቹ ጋር እየተለያየ የሚገኘው ኢትዮጵያ ቡና ከአቤል እንዳለ ጋር በስምምነት መለያየቱን ክለቡ አረጋግጦልናል። በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ የተገኘው እና በደደቢት እና በቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫውቶ ያሳለፈው አቤል እንዳለ የሁለት አመታት ቀሪ ኮንትራት እያለው ነው ከኢትዮጵያ ቡና ጋር በስምምነት የተለያየው።

በሌላ ዜና ኢትዮጵያ ቡና በቀጣይ ቀናት በተለይ ከኋላ መስመር ክፍሉን ለማጠናከር ተጨማሪ ተጫዋቾች ያስፈርማል ተብሎ ይጠበቃል።