ሀዋሳ ከተማ የጋናዊውን ግብ ጠባቂ ውል አራዝሟል

ሀይቆቹ የግብ ጠባቂው መሐመድ ሙንታሪን ውል ለተጨማሪ ዓመት አድሰዋል።
ከሰሞኑ በአዳዲስ ተጫዋቾች ዝውውር ተጠምደው የሰነበቱት ሀዋሳ ከተማዎች አሁን ደግሞ ወደ ነባር ተጫዋቾች ፊታቸውን አዙረዋል። በዚህም የጋናዊው ግብ ጠባቂ መሐመድ ሙንታሪን ቆይታ ለተጨማሪ ዓመት ማደሳቸው ታውቋል።

ወደ ኢትዮጵያ ከመጣ በኋላ በጅማ አባጅፋር እና ሀድያ ሆሳዕና በመጫወት ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ጋር መተዋወቅ የቻለው ቁመታሙ ግብ ጠባቂ ዘንድሮ ባሳለፈበት ክለብ ለቀጣዮቹ አንድ ዓመት ግልጋሎት የሚሰጥ ይሆናል።

በተያያዘ ዜና ሀዋሳ ከተማ በውሰት ለጅማ አባጅፋር ሰጥቶት የነበረውን ግብ ጠባቂ አላዛር ማርቆስ ወደ ክለቡ መመለሱን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።