ኢትዮጵያ መድን የመስመር ተከላካይ አስፈርሟል

ፕሪምየር ሊጉን ዳግም የተቀላቀለው ኢትዮጵያ መድን አብዱልከሪም መሐመድን ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል።

ከከፍተኛ ሊግ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ካደጉ ሦስት ክለቦች መካከል ቡድኑን በማጠናከር ስራ ላይ ቀዳሚ የሆነው ኢትዮጵያ መድን በርካታ ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ እየቀላቀለ ይገኛል። ከደቂቃዎች በፊት ደግሞ የመስመር ተከላካዩ አብዱልከሪም መሐመድን በእጁ ማስገባቱን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

የቀድሞ ደቡብ ፖሊስ፣ ሀዋሳ ከተማ፣ ሲዳማ ቡና፣ ኢትዮጵያ ቡና እና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋች የነበረው አብዱልከሪም ዘንድሮ በፋሲል ከነማ መለያ የውድድር ዓመቱን ቢጀምርም በግማሽ ዓመት በስምምነት ተለያይቶ ነበር። በ2010 የሊጉ ኮከብ ተጫዋች ተብሎ የተመረጠው ተጫዋቹ በአንድ ዓመት ውል መድንን መቀላቀሉ ተረጋግጧል።