ዛምቢያ 2017፡ የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን ለእሁዱ ጨዋታ ዝግጅቱን ቀጥሏል

የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን በዛምቢያ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ የማጣርያ ጨዋታውን በመጪው እሁድ ከሶማልያ ጋር ያደርጋል፡፡ ለጨዋታው የሚያደርገውን ዝግጅትም ቀጥሏል፡፡

ቡድኑ ከ2 ሳምታት በፊት ለ38 ተጫዋቾች ጥሪ በማድረግ ዝግጅት የጀመረ ቢሆንም በሂደት በርካታ ተጫዋቾች ቡድኑን በመቀላቀላቸው የመለየት ስራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡ በአሁኑ ሰአት 25 ተጫዋቾች በቡድኑ ውስጥ ሲቀሩ በትላንትናው እለት ለጨዋታው የሚያደርገውን ዝጅግት በተሟላ ሁኔታ ጀምሯል፡፡

አሰልጣኝ ግርማ ሃብተዮሃንስ በዛሬው የልምምድ ፕሮግራም ተጫዋቾችን ለሁለት በመክፈል ቋሚ ተሰላፊ ሊሆኑ የሚችሉ ተጫዋቾችን በሚለይ መልኩ ረጅም ደቂቃዎች የፈጀ የልምምድ ጨዋታ አጫውተዋል፡፡

ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድናችን ከፕሪሚየር ሊግ ፣ ከፍተኛ ሊግ ፣ ብሄራዊ ሊግ እና ተስፋ ቡድኖች የተውጣጡ 25 ተጫዋች ሲኖሩት ከሁለት በላይ ተጫዋች ያስመረጡ የከፍተኛ ሊግ ክለቦች በዚህ ሳምት የሚያደርጉት ጨዋታ ለሌላ ጊዜ ይዛወራል ተብሏል፡፡

ብሄራዊ ቡድናችን በመጨው እሁድ የመጀመርያውን ጨዋታ አዲስ አበባ ስታድየም ላይ ሲያደርግ ሩዋንዳዊያን ዳኞች ጨዋታውን ይመሩታል፡፡ የመልሱ ጨዋታ ደግሞ ሚያዝያ 15 ወይም 16 ሲደረግ ጨዋታው በሶማልያ አልያም በገለልተኛ ሃገር እንደሚካሄድ ካፍ እስካሁን አላሳወቀም፡፡

በ20 አመት በታች ቡድኑ ዙርያ የአሰልጣኝ ግርማ እና የተጫዋችን አስተያየቶች ከጨዋታው በፊት የምናቀርብላችሁ ይሆናል፡፡

PicsArt_1459426002697

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *