የሉሲዎቹ አሠልጣኝ ወደ ለንደን አምርተዋል

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል ወደ እንግሊዝ ጉዞ ጀምረዋል።

የኢትዮጵያ ሴቶች ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድንን ይዘው የሴካፋ ባለድል የሆኑት አሠልጣኝ ፍሬው በቅርቡ ዋናውን ቡድን በመያዝ በቀጠናው ውድድር ላይ ተሳትፈው ሦስተኛ ደረጃን ይዘው ማጠናቀቃቸው ይታወሳል። አሠልጣኙ በአሁኑ ሰዓት ውድድር ላይ ባይገኙም ወደ እንግሊዝ ጉዞ እንደጀመሩ ለማወቅ ተችሏል።

የኢትዮጵያዊያን የስፖርት ፌስቲቫል በእንግሊዝ የሚከናወን ሲሆን ለዚህ ዝግጅት አሠልጣኙ በክብር እንግድነት ተጋብዘው እንዳመሩና ለአስር ቀናት እዛው እንግሊዝ ለንደን እንደሚቆዩ ታውቋል።