ፀጋሰው ድማሙ ወደ አዲስ አዳጊዎቹ አምርቷል

በርከት ያሉ አዳዲስ ተጫዋቾች እያስፈረሙ የሚገኙት ኢትዮጵያ መድኖች ዛሬ ረፋድ ላይ ደግሞ የመሀል ተከላካይ ወደ ስብስባቸው ቀላቅለዋል።

በገበያው ቡድናቸውን እንደ አዲስ ለማዋቀር ጥረት እያደረጉ የሚገኙት ኢትዮጵያ መድኖች እስካሁን ስምንት ተጫዋቾች ያስፈረሙ ሲሆን ዛሬ ረፋድ ደግሞ ዘጠነኛ ተጫዋቻቸውን አግኝተዋል።

ከዚህ ቀደም በሀዲያ ሆሳዕና እንዲሁም በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ደግሞ በሀዋሳ ከተማ ቆይታን ያደረገው የመሀል ተከላካዩ ፀጋሰው ድማሙ ከሀዋሳ ከተማ ጋር ቀሪ የአንድ ዓመት ውል ቢኖረውም በስምምነት አቋርጦ በአዲሱ የውድድር ዘመን ደግሞ በኢትዮጵያ መድን ሲጫወት የምንመለከተው ይሆናል።

እስካሁን ዋና አሰልጣኙን በይፋ ያላስተዋወቀው ቡድኑ በቀጣይም ተጨማሪ ተጫዋቾችን ወደ ቡድኑ ይቀላቅላል ተብሎ ይጠበቃል።