ቻርልስ ሪባኑ በመጨረሻም የባህር ዳር ተጫዋች ሆኗል

በክረምቱ የዝውውር መስኮት በንቃት እየተሳተፉ የሚገኙት ባህር ዳር ከተማዎች ከዚህ ቀደም ቅድመ ስምምነት ስለመፈፀሙ የዘገብነውን ናይጄሪያዊውን አማካይ ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ከሰዓታት በፊት የዓብስራ ተስፋዬን ያስፈረሙት ባህር ዳር ከተማዎች ከደቂቃዎች በፊትም ናይጄሪያዊውን የተከላካይ አማካይ ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

በ2013 የኢትዮጵያ እግርኳስ የተዋወቀው አማካዩ በከፍተኛ ሊግ በሀምበርቾ ዱራሚ ቆይታ የነበረው ሲሆን በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ ቡድን ውስጥ ነጥረው ከወጡ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ያደረገውን ብቃት አሳይቷል።

ጥሩ የማይባል የውድድር ዘመን ያሳለፉት ባህር ዳር ከተማዎች በቀጣዩ የውድድር ዘመን ተጠናክረው ለመቅረብ የተለያዩ ተጫዋቾችን ያስፈረሙ ሲሆን በቀጣይም የተወሰኑ ተጫዋቾችን ይጨምራሉ ተብሎ ይጠበቃል።