የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ መካከለኛ ዞን ተስተካካይ ሁለት ጨዋታዎች (9ኛ ሳምንት ላይ መካሄድ የነበረባቸው) ትላንት ተካሂደው ደደቢት እና ንግድ ባንክ በድል ጉዟቸው ቀጥለዋል፡፡ ቀጣይ ተስተካካይ ጨዋታዎችም ከሰኞ ጀምረው ይካሄዳሉ፡፡
ንግድ ባንክ እቴጌን በሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እቴጌን 8-0 በመርታት ደረጃውን ወደ 2ኝነት ከፍ ማድረግ ችሏል፡፡ ለሃምራዊ ለባሾቹ ረሂማ ዘርጋ አራት ፣ ቅድስት ቦጋለ እና ሽታዬ ሲሳይ ሁለት ሁለት ግቦች አስቆጥረዋል፡፡ ረሂማ ትላንት ያስቆጠረቻቸውን ግቦች ጨምሮ የውድድር ዘመኑ ግብ መጠኗን ወደ 9 ስታሳድግ ተሸናፊው እቴጌ ከ10 ጨዋታዎች 50 የግብ እዳ ለመሸከም ተገዷል፡፡
ደደቢት በድል ሪኮርዱ ቀጥሏል
ደደቢት ትላንት በከፍተኛ ትግል ዳሽን ቢራን ካሸነፈ በኋላ 9ኛ ተከታታይ ድሉን አስመዝግቧል፡፡ ደደቢት በብርቱካን ገብረክርስቶስ ግብ ቀዳሚ መሆን ሲችል ዳሽን ተቀይራ በገባችው ፅዮን ግብ አቻ መሆን ችሎ ነበር፡፡ የጨዋው የመጨረሻ 20 ደቂቃዎች ከፍተኛ ፉክክር የተስተናገደበት ሲሆን በመጨረሻም ሎዛ አበራ የዳሽን ተከላካዮች ስህተትን ተጠቅማ የደደቢትን የድል ግብ አስቆራለች፡፡ በሁሉም የሊጉ ጨዋታዎች ግብ ማስቆጠር የቻለችው ሎዛ በ8 ጨዋታ 22 ግቦች በማስቆጠር ከፍተኛ ግብ አግቢነቱን መምራቷን ቀጥላለች፡፡
ቀጣይ ጨዋታዎች
በ10ኛ እና 11ኛ ሳምንት ያልተካሄዱ ቀሪ ጨዋታዎች ከሰኞ ጀምረው ይካሄዳሉ፡፡ የመጀመርያው ዙርም መጋቢት 30 ፍፃሜውን ያገኛል፡፡
እሁድ መጋቢት 25 ቀን 2008
09፡00 ዳሽን ቢራ ከ ቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ (ጎንደር)
ሰኞ መጋቢት 26 ቀን 2008
09፡00 ደደቢት ከ መከላከያ (አአ)
11፡00 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (አአ)
አርብ መጋቢት 30 ቀን 2008
09፡00 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ልደታ (አአ)
11፡00 ኤሌክትሪክ ከ ደደቢት (አአ)
የደረጃ ሰንጠረዥ
ለማስታወስ ያህል የደቡብ-ምስራቅ ዞን ፕሪሚየር ሊግ 1ኛ ዙር ከወር በፊት ተጠናቋል፡፡ የደረጃ ሰንጠረዡም ይህንን ይመስላል፡-