የመስመር ተከላካዩ ወደ ኤሌክትሪክ አምርቷል

ለኢትዮጵያ መድን ለመጫወት ተቃርቦ የነበረው ጌቱ ኃይለማርያም ሌላኛውን አዳጊ ክለብ ተቀላቅሏል።

በርከት ያሉ ተጫዋቾቹን ውል እያራዘመ እና አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ እያካተተ የሚገኘው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከደቂቃዎች በፊት የግብ ጠባቂውን ፍቅሩ ወዴሳ እና የኃይሌ ገብረትንሳይን ዝውውር ያጠናቀቀ ሲሆን አሁን ደግሞ የመስመር ተከላካዩን ጌቱ ኃይለማርያም ማስፈረሙን ሶከር ኢትዮጵያ አውቃለች።

ከከፍተኛ ሊግ ጀምሮ በሰበታ ከተማ ጥሩ ጊዜያትን ማሳለፍ የቻለው የቀኝ መስመር ተከላካዩ ጌቱ ኃይለማርያም ኢትዮጵያ መድን ለመጫወት ተቃርቦ የነበረ ቢሆንም በስተመጨረሻ ለአንድ ዓመት በኤሌትሪኮች ቤት የሚያቆየውን ስምምነት ፈፅሟል። በዛሬው ዕለት ለቡድኑ የፈረሙት ኃይሌ እና ጌቱ ቀዳሚ ቦታን ለማግኘት የሚያደርጉት ፉክክርም ይጠበቃል።