ሲዳማ ቡና ከግብ ዘቡ ጋር በስምምነት ተለያይቷል

በተጠናቀቀው ዓመት ሲዳማ ቡናን በመቀላቀል ግልጋሎት የሰጠው ግብጠባቂ ከክለቡ ጋር በስምምነት መለያየቱ ተረጋግጧል።

የ2015 ቅድመ ዝግጅታቸውን በመቀመጫ ከተማቸው በሆነችው ሀዋሳ ከቀናት በፊት የጀመሩት ሲዳማ ቡናዎች ከግብ ጠባቂያቸው ተክለማርያም ሻንቆ ጋር በስምምነት መለያየታቸውን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

በሀላባ ከተማ፣ በአዲስ አበባ ከተማ ፣ ሀዋሳ ከተማ እና በኢትዮጵያ ቡና እንዲሁም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጫወት ያሳለፈው ተክለማርያም በያዘነው ዓመት ሲዳማ ቡናን ቢቀላቀልም ቀሪ የአንድ ዓመት ኮንትራት እየቀረው በስምምነት መለያየቱ ታውቋል።