ዋሊድ አታ ለኦስተርሰንድስ የመጀመሪያ የሊግ ጨዋታውን አድርጓል

የስዊድን ሊግ የ2016 የውድድር ዘመን ባሳለፍነው ሳምንት ተጀመሯል፡፡ በመጋቢት ወር የሊጉ ክለብ ኦስተርሰንድስን የተቀላቀው ኢትዮጵያዊው የመሃል ተከላካይ ዋሊድ አታም ክለቡ በሊጉ መክፈቻ ከሜዳው ውጪ ነጥብ ተጋርቶ በተመለሰበት ጨዋታሙሉ 90 ደቂቃ መጫወት ችሏል፡፡

በስዊድን መዲና በሆነችው ስቶኮልም በሚገኘው በቴሌ2 አሬና በተደረገው ጨዋታ አዲስ መጪው ኦስተርሰንድንስ ከሃመርባይ ጋር 1-1 ተለያይቶ ተመልሷል፡፡ ባለሜዳዎቹ ጨዋታው በተጀመረ በ14ኛው ደቂቃ በላርስ ሴትራ ግብ መምራት የቻሉ ሲሆን ሳማን ጎዶስ በ35ኛው ደቂቃ ኦስተርሰንድስን አቻ አድርጓል፡፡ ዋሊድ ካልተሳካ የስድስት ወራት የአንካራ ቆይታ በኃላ በስዊድን ሊግ ያደረገው የመጀመሪያው የሊግ ጨዋታው ሲሆን ከሁለት ሳምንታት በፊት በስዊድን ዋንጫ ጨዋታ ላይ መሰለፍም ችሏል፡፡

የሊጉ ሁለተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ ቀጥለው ሲካሄዱ ኦስተርሰንድስ በሜዳው ኤአይኬን ያስተናግዳል፡፡ እንግሊዛዊው ግርሃም ፖተር ዋሊድ የቀድሞ ክለቡን ኤአይኬን ለመግጠም በቋሚ አሰላለፍ ውስጥ ያስገቡታል ተብሎም ይጠበቃል፡፡ ዋሊድ ከሌላኛው ኢትዮጵያዊ ተጫዋች የሱፍ ሳሌ ጋር በኤአይኬ የሊጉን ዋንጫ ማንሳቱ የሚታወስ ነው፡፡

ሊጉን ሁለት ጨዋታ ያደረገው ጎተንበርግ በስድስት ነጥብ ሲመራ አንድ ጨዋታ የሚቀረው ኦስተርሰንድስ በ1 ነጥብ 12ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

 

ፎቶ – ከዋሊድ አታ የፌስቡክ ገጽ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *