የአሠልጣኞች አስተያየት | ሀዲያ ሆሳዕና 0-0 ፋሲል ከነማ

👉”ሽንፈት በስነ-ልቦናችን ላይ ጫና ስለሚፈጥር ለዛ ነው አስጠብቀን ያለንን ይዘን ለመውጣት እና በምናገኛቸው አጋጣሚዎች ጎል አስቆጥረን ለማሸነፍ ጥረት ያደረግነው” ያሬድ ገመቹ

👉”እርግጠኛ ነኝ በመጣንበት መንገድ ሁለተኛውን ዙር የምቀጥል አይመስለኝም ፤ ብዙ ማረም የሚገቡን ስህተቶች አሉ” ሙሉቀን አቦሃይ

ያሬድ ገመቹ – ሀዲያ ሆሳዕና

ስለ ጨዋታው…

ጨዋታው ጥሩ እና ፈጣን እንቅስቃሴ ነበር። እንደ አጠቃላይ እነሱ ጥሩ ናቸው ፤ እኛም ጥሩ እንቅስቃሴ ነበር ያደረግነው።

በሁለተኛው አጋማሽ የማጥቃት እንቅስቃሴያቸው ስለመቀዛቀዙ…

አንዷን ነጥብ ማስጠበቅ አለብን። ምክንያቱም ከተሸነፍን ሌሎች ከእኛ በታች ያሉ ቡድኖች በቅርበት ስላሉ ይሄን ነጥብ መጣል የለብንም ፤ ሽንፈት በስነልቦናችንም ላይ ጫና ስለሚፈጥር ለዛ ነው አስጠብቀን ያለንን ይዘን ለመውጣት እና በምናገኛቸው አጋጣሚዎች ጎል አስቆጥረን ለማሸነፍ ጥረት ያደረግነው።

የአጥቂ ቦታ ላይ ስላሉ ተጫዋቾቻቸው…

ትልቁ ነገር ጎል ላይ መድረስ ነው ያን የአጨራረሱን ነገር ወደፊት በሥራ የምናስተካክለው ይሆናል። ነገር ግን በርካታ ኳሶችን እያባከንን ነው። የጎል አጋጣሚዎችንም እየፈጠርን አጋጣሚዎች እያባከንን ነውና እዛ ላይ ጠንክረን መሥራት ይጠበቅብናል።

በዕረፍት ጊዜው ለማስተካከል ስላሰቡት ነገር…

በዕረፍት ቀናት ጠንካራ የአጨራረስ ሥራዎችን መሥራት አለብን ፤ ምክንያቱም ጎል ማስቆጠር አልቻልንም። ባዬ ገዛኸኝ በቀይ ካርድ ከወጣ በኋላ ጎል የማስቆጠራችን ነገር ደክሟል። ስለዚህ እዛ ላይ ከፍተኛ ትኩረት እና ሥራ ይፈልጋል። የማሻሻያ ሥራዎች ሠርተን ለቀጣይ ጥሩ ተፎካካሪ ሆነን መቀጠል ነው ሀሳባችን።

ሙሉቀን አቦሃይ (ምክትል አሠልጣኝ) – ፋሲል ከነማ

ስለጨዋታው…

እንደታየው ከመጀመሪያው ጀምሮ ቀጥተኛ ነበር። እኛም ለዛ የሚሆን አጨዋወት ነበር ልንጠቀም የፈለግነው። ሁለተኛ ኳስ ማሸነፍ ላይ ደካሞች ስለነበርን ጨዋታውን በተወሰነ መልኩ ከባድ አድርጎብናል።

የአሰልጣኝ ኃይሉ ነጋሽ አለመኖር ስላለው ተፅዕኖ…

ትናንት ነው የሄደው እስከትናንት ድረስ ቡድኑ ጋር ነበር። ምናልባት ዛሬ ጨዋታውን መምራት ነው ያልቻለው እንጂ እስከትናንት ነበር። በተወሰነ መልኩ ግን የዛሬው ጨዋታ ላይ ቡድኑ ላይ የሚፈጥረው ነገር ይኖራል።

በዕረፍቱ ጊዜ መሥራት ስላሰቡት ነገር…

እርግጠኛ ነኝ በመጣንበት መንገድ ሁለተኛውን ዙር የምቀጥል አይመስለኝም ፤ ብዙ ማረም የሚገቡን ስህተቶች አሉ። አርመን እንመጣለን ብዬ አስባለሁ።