ታክቲካዊ ትንታኔ : ኢትዮጵያ ቡና 3-1 አርባ ምንጭ ከነማ

ኢትዮጵያ ቡና 3-1 አርባ ምንጭ ከነማ
ህዳር 21/2014 ዓ.ም

በሚልኪያስ አበራ
‹‹ አዬ ሀዬ ጋሞቶ (ና እንደ አንበሳ)›› በሚል ደማቅ የአርባምንጭ ደጋፊዎች ህብረ ዝማሬ እና የዘወትር የአዲስ አበባ ስታዲየም አድማቂዎች በሆኑት የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ተወዳጅና አነሳሽ መዝሙር ‹‹ቡና ገበያ አደገኛ!›› የደመቀው የእሁድ የስታዲየም ድባብ ደስ የሚል ነበር፡፡ እንግዳው ቡድን አርባ ምንጭ ከነማ በዚህ አመት በተደጋጋሚ ሲጠቀምበት በተስተዋለው 4-4-2 ዳይመንድ ጨዋታውን የጀመረ ሲሆን ባለሜዳው የኢትዮጵያ ቡና ደግሞ 4-1-3-2ን በጫወታው አብዛኛውን ክፍለ ጊዜ ተጥቅሟል፡፡(ቡና በ73ኛው ደቂቃ መስኡድ ተቀይሮ እስከወጣበት ጊዜ ድረስ ) እየተጫወተ የነበረበትን ፎርሜሽን (የተጫዋቾች የሜዳ ላይ አደራደር) ለመረዳት እጅግ አዳጋች ነበር፡፡ ቡድኖች እየተጨወቱ ያሉበትን ቅርፅ ለመረዳት ጊዜ አስቸጋሪ ነው፡፡ ይህም በፕሪምየር ሊጉ በሚሳተፉ ቡደኖች ላይ የሚታይ አንዱ ችግር ነው፡፡ በዚህ ጨዋታ የቡናን መደበኛ ቅርፅ ለመረዳት ከSoccer Ethiopia ባልደረባዬ አብርሃም ጋር ለረዥም ጊዜ ጠብቀናል፡፡ ይህም በቀላሉ የቡድኖችን የተጨዋቾች የሜዳ ላይ አደራደር Pattern ለማወጣት አስቸጋጋ በመሆኑ ነው፡፡ (ምስል 1)
Bunna 3-1 AMK (1)
የቡናዎች 4-1-3-2 እና የአርባ ምንጮች 4-4-2 ዳይመንድ
የቡናዎችን ፎርሜሽን 4-1-3-2 ለማለት የተገደድኩት የተከላካይ አማካዩ ጋቶፕ ፓኖም ከፊቱ ካሉት አማካዮች ኤልያስ (በቀኝ )፤ መስኡድ መሃል እና ጥላሁን (ግራ) ርቆ ስለተጫወተ ብቻ ሳይሆን በአርባ ምንጩ 18 (የዳይመንዱ የላይኛው ጫፍ ላይ የተጨወተ) በከፍተኛ ሁኔታ press ስለተደረገም (ተጭኖት ስለተጫወተ) ከፊቱ ካሉት አማካዮች ይልቅ ከኋለው ካሉት ተከላካዮች ቀርቦ እንዲቸወትና እንዲነጠል ተደርጓል፡፡ ይህም የአርባ ምንጩ ሙሉአለም መስፍን (ከኋላ የዳይመንዱ ጫፍ ላይ የተሰለፈ) ወደፊት ተጠግቶ የዳይመንዱን ቁመት ለማጥበብና ከአጥቂ አማካዩ ጋር ተቀራርቦ በመጫወት ቡናዎች ላይ የመሀል ሜዳ የበላይነት በማስገኘት ሞክሯል፡፡ ሆኖም 3ቱ የቡና አማካዮች በተለይም ኤልያስና መስኡድ በአርባ ምንጭ ተከላካዮችና አማካዮች መካከል የሚፈጠረውን ሰፊ ክፍተት (Between the lines; through the channels) በመጠቀም ተደጋጋሚ የጐል ሙከራና ጫና ሲፈጥሩ ታይተዋል፡፡ በእርግጥ አልፎ አልፎም ቢሆን የአሰልጣኝ አለማየሁ መኮንን ልጆች (አርባምንጮች) ይህንን ችግራቸውን ለመቅረፍ ተከላካዮቻቸውን ወደ መሃለኛው የሜዳ ክፍል በመላክ (High-line defense) በመስራት በይበልጥም ከኳስ ቁጥጥር ጋር እና ከማጥቃት እንቅስቃሴያቸው ጋር አዛምደው ክፍተቱን ለማጥበብ ሞክረዋል፡፡
አርባ ምንጮች በመጀመርያው 45’ ውስጥ የቡናን የግራ መስመር በተደጋጋሚ ለማጥቃት እንቅስቃሴያቸው ሲጠቀሙበት ነበር፡፡ ምን አልባትም 18ቱ ፣ ተመስገን ዱባ እና ትርታዬ ደመቀ ብዙውን ግዜውን በመከላከል ስራ ላይ ያተኮረውን እና በትርታዬ አማካኝነት (Press) የተደረገውን የቡናው የግራ መስመር ተከላካይ 29 ላይ ብዙ በመሆን (over load በማድረግ) ተጫዋቹን ጫና ውስጥ ጥለውት ነበር፡፡ይህንን ማድረጋቸው ሁለት ጥቅሞችን አስገኝቶላቸዋል፡፡የመጀመርያው 29ኙ ወደ ተጋጣሚ ሜዳ (አርባ ምንጭ) ክልል ገብቶ ለቡና የማጥቃት እንቅስቃሴ አስተዋፅኦ እንዲያደርግ የገደቡት ሲሆን ሌላኛው ደግሞ በዘያው መስመር በማጥቃት አጨዋወቱ እና ለመከላከል ተሳትፎ የሚተወቀውን ጥላሁን ወልዴን ከተከላካዮ በመነጠል በመካከላቸው ሰፊ ክፍተት እንዲፈጠር አድርገዋል፡፡ይህም ጥላሁንን ወደ ኋላ ተስቦ እንዲጨወትና 29ኙን እንዲያግዝ ( በብዛት ) አድርጐታል፡፡ በዚህም አርባ ምንጮች ሰፊ የመጫወቻ ክፍተትን እንዲያገኙ ሆነዋል፡፡ በ7ኛው ደቂቃ ላይ በረከት ለአርባ ምንጮች የመሪነት ጐል ያገባው ከዚሁ የቡና የግራ መስመር በተመሰረተ ኳስ ነበር፡፡በርግጥ ብዙም ሳይቆይ ቡናዎች የአርባምንጩ አብዮት ደመቀ ትቶት የሄደውን ሰፊ ቦታ ተጠቅመው ቢንያም አሰፋ አቻ አድርጓቸዋል፡፡ በቀኝ መስመር ዴቪድ በሻህ ከዚህ ቀደም እንደነበሩት ጨዋታዎች ቡድኑ የማጥቃት እንቅስቃሴ ላይ ቀጥተኛ የሆነ ተሳትፎ ሲያደርግ አስተወለናል፡፡ የአርባ ምንጩ 16 ከፍተኛ የትኩርት ማጣት ይነበብበት ነበር፡፡ ለማጥቃት ወደ ፊት ሲሄድ ከኋላ የሚተወውን ሰፊ ክፍተት ያገናዘበ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ልንመለከት አልቻልንም፡፡ ይህን ድክመትም ቡናዎች በዴቪድ ፤ ኤልያስና መስኡድ አማካኝነት ሲጠቀሙበት ታይተዋል፡፡አርባ ምንጮች በደካማው የቡና የግራ መስመር 37ኛው ደቂቃ አካባቢ የተመሰረተችን ኳስ አጥቂው ተመስገን ዳባ በሁለቱ የቡና የመሃል ተከላካዮች መሃል አግኝቶ የሞከራት ጥሩ የማግባት ሙከራ የቡናን ግራ መስመር ይበልጥ ተጋላጩ እንደነበር ከሚያመለክቱ ማሳያዎች አንዱ ነበር፡፡
( ምስል 2 )
Bunna 3-1 AMK (2)
የቡና ሁለቱ አጥቂዎች ማዕዘናዊ እንቅስቃሴ(Geometrical Movement)
ቢንያም አሰፋኖና አስቻለው ግርማ በጨዋታው የነበራቸው ሚና እጅግ ወሳኝ ነበር፡፡ ተጫዋቾች በሜዳ ላይ ሲያሳዩ የነበረው ከተገጣሚ የመስመር ተከላካዮች ጀርባ በመገኘት እንዲሁም በተጋጣሚ የመሃል ተካላካዮችና የመስመር ተከላከዮች መካከል በመግባት ሰፊ የመጫወቻ ክፍተትን በመፍጠር በመጠቀምም የተዋጣለት እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ለማየት ችለናል፡፡ ቢንያም ባብዛኛው ወደ ግራው መስመር አዘንብሎ ከኋላው ላሉት አማካዮች ክፍተትን እየፈጠተና የአርባ ምንጭን የቀኝ መስመር ተከላካይ (ታገል አበበን) እየተጫነ (Press እያደረገ) አስቻለው ደግሞ ወደኋላ እየተሳበ በሜዳው ወርድ በግራና በቀኝ ፈጣን እንቅስቃሴዎችን እያደረገ የአርባ ምንጭን ተከላካዮች ላይ በተደጋጋሚ የመከላከል ቅርፅቸው ላይ ችግር ሲፈጥር ነበር፡፡
(ምስል 3 )

Bunna 3-1 AMK (3)

ከዕረፍት መልስእስከ 64ኛው ደቂቃ ድረስ ጨዋታው በተመሳሳይ ውጤትና የቡድኖዎች የአጨዋወት ቅርፅ ቢጓዝም ጥላሁን በእንቅስቃሴው መጠነኛ ለውጥ አሳይቷል፡፡ ተጨዋቱ በነፃ ሚና (Free role) በተደጋጋሚ ወደ መህል ሜዳ በመግባት ቡድኑን ሲረዳ ተስተውሏል፡፡ ነገር ግን ከኋላ የነበረው ፉልባክ ላይ ጫናን ሲያስከትል የነበረ እንቅስቃሴ ሲያደርግም ታይቷል፡፡ አርባ ምንጫ 64ኛው ደቂቃ ላይ 18ቱን አስወጥተው ጌቼሮን ማስገባቱ የመስመር (የቀኝ) ላይ የማጥቃት አማራጭን ጨምሮለታል፡፡ ትርታዬ ደመቀም ከመስመር ተነስቶ (ከቀኝ ) ወደ ዳይመንድ ጫፍ በመሸጋጋር የተሻለ እንቅስቃሴ ለማድረግ ችሏል፡፡ቡናዎችም በ66ኛው ደቂቃ ላይ በጨዋታው ብዙም ጥሩ ሲንቀሳቀስ ያልታየው ጋቶችን አስወጥተው ሚካኤል በየነን አስገቡ፡፡ ሚካኤል ከጋቶች የበለጠ ወደፊት ተጠግቶ የአርባምንጭ የመሀል ሜዳ የበላይነት ላይ መጠነኛ ችግር ሲፈጥር ነበር፡፡አሰልጣኝ ጥላሁን መንገሻ በ73ኛው ደቂቃ ላይ መሱድን በአጥቂው ሻኩሪ መቀየራቸው ጥሩ እይታ እንደነበር ሳይጠቀስ መታለፍ የለበትም፡፡ ምክንያቱም ምርጥ የቴክኒክ ክህሎት ፤ የታክቲክ ግንዛቤና የጥሩ ስነ-ምግባር ባለቤት የሆነው መስኡድ በዚህ ጨዋታ አመርቄ እንቅስቃሴ ማሳየት ተስኖት ታይቷል፡፡ የቡናው አምበል በተደጋጋሚ በሜዳው ላይ ያለው ሚና ምን እንደነበር ግራ በሚገባ መልኩ ኳስ ያለበትን ቦታ ያማከለ (Ball-oriented movement) እንቅስቃሴ ስያደርግ ተስተውሎል፡፡ በቀኝ መስመር አዘንብሎ መጫወቱ በቦታው (Over load) በጥቂት የመጫወቻ ስፍራ የመታጨቅ ችግርን ሲፈጥር ተስተወሏል፡፡ ኳስ ወዳለችበት ወደየትኛውን አቅጣጫ መንቀሳቀሱም ጉልበቱን የሚባክንበት እና የታክቲክ ግንዛቤውን የሚገድልበት ይመስለኛል፡፡ ስለዚህም ቦታን ጠብቆ የመጫወት ኃላፊነት (positional-play) ላይ ቢያተኩር ለራሱም ለቡድኑም አሁን እያበረከተ ካለው አስተዋፅኦ በላይ ሊያበረክት እንደሚችል እምነቴ ነው፡፡ ቡናዎች በዚህኛው ቅያሪ ሻኩሪ የአጥቂነቱን ስፍራ እንዲይዝና አስቻለው ወደ ኋላ እንዲመለስና የመስመር አማካይ እንዲሆን በማድረግ ወደ 4-4-2 የሚያመዝን ቅርፅ ያዙ፡፡ በ76ኛው ደቂቃ ላይም ቢንያም አሰፋ ወደ ግራ መስመር ተጠግቶ ፤ የበረኛውን ቁመትና የለበትን ቦታ ተመልክቶ በግራ እግሩ ከርቀት ያስቆጠራት ጐል የምትደነቅ ነበረች፡፡

ከዚህ ጐል መቆጠር በኋላ አርባ ምንጮች በ80ኛው ደቂቃ ላይ ሁለት ቅያሪዎችንና የቦታ ለውጦችን አደረጉ፡፡ምንተስኖት ወጥቶ 6 ገባ፤ ታገልንም በ10 ቁጥሩ ቀየሩ፡፡ ይህም ጌቼሮን ወደ ቀኝ መስመር ተከላካይነት አሸጋገረው፡፡ ብዙ ተጨዋቾችን ወደ ቡና የግብ ክልል በመላክም መጠነኛ የማጥቃት እንቅስቃሴ ለመፈጠር ቢሞክሩም ጐል ማስቆጠር አልቻሉም፡፡ ይልቁንም በዚህ ሂደት በተከላካዮቻቸውና በአማካዮቻቸው መካከል የነበረውን ሰፊ ክፍተት (Between the lines) ተጠቀሞ ጥላሁን ወልዴ የቡና 3ኛ ጐል 84ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጠረ፡፡ ይህ ጐል ሲቆጠር የአርባ ምንጮ ተከላካዮች ከፊታቸውም በመከላከላቸውም ሰፊ ክፍተትን ፈጥረው ነበር፡፡ ጥላሁንም ተረጋግቶ ኳሷን ከመረብ ሊያሳርፋት ችሏል፡፡ (ምስል 4)

Bunna 3-1 AMK (4)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *