ቁመታሙ አጥቂ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሷል

ማሊያዊው አጥቂ ወደ ቀድሞ ክለቡ የተመለሰበትን ዝውውር አገባዷል።

\"\"

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በአሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው የሚመሩት ባህርዳር ከተማዎች ኦሴ ማውሊን ባሰናበቱበት የአጥቂ ክፍላቸው ላይ የቀድሞው አጥቂያቸውን ፊፋ በሚያዘው ህግ መሠረት በነፃ ዝውውር ማስፈረማቸው ታውቋል።

\"\"

ወደ ቀድሞው ክለቡ የተመለሰው የ31 ዓመቱ ማሊያዊው አጥቂ ማማዱ ሲዲቤ ነው። 2010 ላይ የሞሮኮውን ራፒድ ኦውድን ለቆ ጅማ አባጅፋርን በመቀላቀል ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ጋር ትውውቅ የጀመረው አጥቂው በመቀጠል በባህርዳር ከተማ ፣ ድሬዳዋ ከተማ እና ሲዳማ ቡና እንዲሁም ያለፉትን ወራት ለሀገሩ ማሊ ክለብ ኤ ኤስ ፓሊስ ያለፈውን ዓመት አሳልፎ በድጋሚ ለቀድሞው ክለቡ ፊርማውን እስከ ዓመቱ መጨረሻ አኑሯል።