ከፍተኛ ሊግ | ኢትዮጵያ ንግድ ሦስት ተጫዋቾችን አስፈርሟል

የምድብ \’ሀ\’ መሪው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለሁለተኛው ዙር የውድድር ጉዞው ሦስት ተጫዋቾችን የስብስቡ አካል አድርጓል።

ከፈረሰ ከአራት ዓመታት በኋላ በድጋሚ ባሳለፍነው ዓመት ወደ ኢትዮጵያ እግርኳስ ብቅ ያለው ንግድ ባንክ የአንደኛውን ዙር ባገባደደው ከፍተኛ ሊግ ምድብ \’ሀ\’ን በ28 ነጥቦች እየመራ የፈፀመ ሲሆን ለሁለተኛው ዙር ጉዞውን ለማሳመር ሦስት ተጫዋቾችን ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል።

\"\"

ቀዳሚው ፈራሚ ፀጋ ዓለማየሁ ከቀድሞ አሰልጣኙ ጋር ዳግም ተገናኝቷል። በገላን ከተማ እና በኢትዮጵያ መድን ከአሰልጣኝ በፀሎት ልዑልሰገድ ጋር አብሮ የሰራው ተጫዋቹ ዘንድሮ በአምበልነት መርቶ ወደ ፕሪምየር ሊግ ባሳደገው መድን ቆይታን ካደረገ በኋላ ንግድ ባንክን ተቀላቅሏል። ኪሩቤል ወንድሙም የክለቡ ሌላኛው አዲስ ፈራሚ ሆኗል። የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹ ከከፍተኛ ሊግ እስከ ዘንድሮ ፕሪምየር ሊግ አጋማሽ በለገጣፎ ለገዳዲ መሳለፍ ችሏል። ሌላኛው የቀድሞው የጅማ አባ ቡና እና የኢትዮ ኤሌክትሪኩ አጥቂ አቤል ሐብታሙ ሦስተኛው የቡድኑ ፈራሚ ሆኗል።‌‌

\"\"