ከፍተኛ ሊግ | ቤንች ማጂ ቡና አምስት ተጫዋቾችን የግሉ አድርጓል

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ሀ ጠንካራ ተፎካካፊ የሆነው ቤንች ማጂ ቡና አዳዲስ ተጫዋቾችን የስብስቡ አካል አድርጓል።

\"\"

በ2015 የከፍተኛ ሊግ ምድብ ሀ ጠንካራ ሆነው ከቀረቡ ክለቦች መካከል ቤንች ማጂ ቡና አንዱ ነው። በአሰልጣኝ መሐመድ ኑርንማ የሚመራው ቡድኑ አንደኛውን ዙር በአንድ ነጥብ ከመሪው ንግድ ባንክ በማነስ በ27 ነጥቦች ሁለተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ የቻለ ሲሆን ለሁለተኛው ዙር የሊጉ መርሀግብር አለብኝ ያለውን ክፍተት ለመድፈን ይረዳው ዘንድ አምስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ቀላቅሏል።

በሰበታ ከተማ እና ያለፉትን ስድስት ወራት ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ቆይታ አድርጎ በስምምነት የተለያየው ግብ ጠባቂው ሰለሞን ደምሴ ፣ በፋሲል ከነማ ከታትኛው ቡድን ከተገኘ በኋላ ረዘም ካለ ዓመት በኋላ የተለያየው ተከላካዩ ዳንኤል ዘመዴን ጨምሮ ያሬድ ወንድማገኝ አጥቂ ከገላን ከተማ ፣ ገዛኸኝ ፍቃዱ አማካይ ከካፋ ቡና እና ስንታየው ሰለሞን አማካይ ከኮልፌ ቀራኒዮ ቡድኑን የተቀላቀሉ አዳዲሶቹ ተጫዋቾች ሆነዋል።

\"\"