የዋልያዎቹ አጥቂ ከጊኒው ጨዋታ ውጪ ሆኗል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተሰላፊውን በጉዳት ምክንያት በማጣቱ በምትኩ ሌላ ጥሪ አድርጓል።

\"\"

የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ አካል የሆኑ ሁለት ጨዋታዎች ከጊኒ አቻው ጋር የሚጠብቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከቀናት በፊት ለተጨዋቾች ጥሪ ማድረጉ ይታወሳል። ከደቂቃዎች በፊት የእግርኳስ ፌዴሬሽኑ ይፋ እንዳደረገው ደግሞ ከፊታችን ረቡዕ ጀምሮ ወደ ልምምድ የሚገባው ብሔራዊ ቡድኑ የወሳኙን አጥቂ አቡበከር ናስርን አገልግሎት እንደማያገኝ ታውቋል።

በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ስብስብ ውስጥ ተካቶ የነበረው የማሜሎዲ ሰንዳውንሱ አጥቂ ከጊኒው ጨዋታ ውጪ የሆነው ከሁለት ወራት በፊት ክለቡ ከኦርላንዶ ፓይሬትስ ጋር በነበረው ጨዋታ በቁርጭምጭሚቱ ላይ ገጥሞት ከነበረው ጉዳት ሙሉ ለሙሉ ባለማገገሙ እንደሆነ ታውቋል። በተጨማሪም በአቡበከር ምትክ በቻን ውድድር ላይ ተሳታፊ የነበረው የኢትዮጵያ መድኑ አጥቂ ኪቲካ ጀማ የዋልያዎቹ አካል እንዲሆን መጠራቱን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ገልጿል።

\"\"