የክልል ክለቦች ሻምፒዮና የሚደረግበት ከተማ ታውቋል

በአንደኛ ሊጉ እና በሴቶች ከፍተኛ ሊግ ላይ የሚሳተፉ ክለቦችን ለመለየት የሚደረገው የክልል ክለቦች ሻምፒዮና የሚጀመርበት ቀን እና ቦታ ተለይቷል።

\"\"

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን በዓመቱ መጨረሻ ከሚደረጉ ውድድሮች መካከል አንዱ የክልል ክለቦች ሻምፒዮና አንዱ ነው። በ2016 የውድድር ዘመን በኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ የሚካፈሉ ስምንት ክለቦችን እና በኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ሁለት ቡድኖችን ለመለየት የሚደረገው ይህ ውድድር በሀዋሳ ከተማ አስተናጋጅነት ለተከታታይ አራተኛ ጊዜ እንደሚደረግ ፌድሬሽኑ ገልጿል። በየክልሎቻቸው የውስጥ ውድድርን ካደረጉ በኋላ በድምሩ ወደ 52 ክለቦችን ያሳትፋል ተብሎ የሚጠበቀው ይህ ውድድር ከሰኔ 3 ጀምሮ በይፋ ይጀመራል።

\"\"