​የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ እጣ ማውጣት ስነስርአት ነገ ይካሄዳል

በአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌሬደሬሽን አዘጋጅነት በየአመቱ ከሚደረጉ ውድድሮች መካከል የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ (ሲቲ ካፕ) የእጣ ማውጣት ስነስርዓት ነገ ረፋድ በኢትዮጵያ ሆቴል ይከናወናል፡፡

በ1998 ዓም መዘጋጀት የጀመረው የሲቲ ካፕ ውድድር ዘንድሮ ለ12ኛ ጊዜ የሚደርግ ሲሆን ስምንት ክለቦች ይሳተፉበታል፡፡ ከመስከረም 27 እስከ ጥቅምት 12 ድረስ በሚደረገው ውድድር በሊጉ ላይ ከሚሳተፉ  አምስት የአዲስ አበባ ክለቦች በተጨማሪ አንድ የከፍተኛ ሊግ ክለብ እና ሁለት ተጋባዥ ክለቦች እንደሚሳተፉ ተረጋግጧል፡፡ በውድድሩ ላይ የአምናው አሸናፊ ኢትዮ ኤሌክትሪክ፣ ደደቢት፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ መከላከያ እና አዲስ አበባ ከተማ የመዲናዋ ክለቦች ሲሆኑ አዳማ ከተማ እና ጅማ አባ ጅፋር በተጋባዥነት እንደሚወዳደሩ ተገልፃል፡፡

ነገ ረፋድ 2 ሰዓት በኢትዮጵያ ሆቴል የእጣ ማውጣት ስነስርዓት እና ለክለቦች የውድድር የደምብ ገለፃ እንደሚደረግ ፌደሬሽኑ ለሚዲያዎች በላከው መግለጫ ሲያስታውቅ ከአንዳድ ክለቦች ጋር የነበሩ ውዝግቦችንም መፍታቱ እና ችግሮችን ተነጋግረው የመፍትሄ ሃሳብ ማስቀመጣቸውን ገልጸዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *