ኢትዮጵያ በአልጄርያ ተሸነፈች

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ በአልጄርያ አቻው 3-1 በሆነ ውጤት ተሸንፏል፡፡ ከዚህ ጨዋታ ቀደም ብሎ ማላዊ ማሊን 2-0 በሆነ ውጤት ማሸነፏ ለብሄራዊ ቡድናችን እንደ መልካም አጋጣሚ ቢወሰድም ኢትዮጵያ ሳትጠቀምበት ቀርታለች፡፡
ግብ በማስቆጠር ቅድሚያውን የያዙት ዋልያዎቹ ሲሆኑ በጨዋታው ጥሩ ሲንቀሳቀስ ያመሸው ኡመድ ኡኩሪ ከፍፁም ቅጣት ምት ሳጥን ውጪ በቀኝ እግሩ መትቶ ግብ አስቆጥሯል፡፡ ነገር ግን የዋልያዎቹ መሪነት የቆየው ለ5 ደቂቃዎች ብቻ ነበር፡፡ ዋሊድ አታ የፈጠረውን ስህተት ተጠቅሞ ሶፊያኔ ፌጉሊ የበርሃ ቀበሮዎቹን አቻ አድርጓል፡፡
ከግቧ መቆጠር በኋላ ሙሉ ለሙሉ ጨዋውን የተቆጣጠሩት አልጄርያዎች በ እና ያሲን ብራሂሚ አማካኝነት 2 ግቦችን አክለው የመጀመርያውን አጋማሽ በ3-1 መሪነት አጠናቀዋል፡፡
በሁለተኛው አጋማሽ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በሽመልስ በቀለ እና ዳዊት ፍቃዱ አማካኝነት ግብ ሊሆኑ የሚችሉ ኳሶችን ሲያመክን በአልጄርያ በኩል ደግሞ ኢስላም ሱሊማኒ በተመሳሳይ ግብ የሚሆን ኳስ አምክኗል፡፡

ምድቡን አልጄርያ ከ5 ጨዋታዎች ሙሉ 15 ነጥብ ይዛ ስትመራ ማሊ እና ማላዊ በ6 ኢትዮጵያ በ3 ይከተላሉ፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *