ሻሸመኔ ከተማ የአሠልጣኙን ውል አራዝሟል

ከረጅም ዓመታት በኋላ ሻሸመኔ ከተማን ወደ ፕሪምየር ሊጉ የመለሱት አሰልጣኝ ፀጋዬ ወንድሙ በዛሬው ዕለት ከክለቡ ጋር ለመቀጠል ውላቸውን አድሰዋል።
\"\"
የ2015 የውድድር ዘመንን በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ላይ ሲወዳደር ዓመቱን ያሳለፈው እና ከ15 ዓመታት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ማደጉን ያረጋገጠው ሻሸመኔ ከተማ ለቀጣዩ የውድድር ዘመን ውጤታማ ካደረጉት አሰልጣኙ ፀጋዬ ወንድሙ ጋር በ2016 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር እንዲቀጥሉ ተስማምቷል። ክለቡ እና አሰልጣኙም በዛሬው ዕለት ለአንድ ዓመት በሚቆይ ውል ስምምነት እንደፈፀሙ ክለቡ ለሶከር ኢትዮጵያ አሳውቋል።

\"\"

የቀድሞው የአቃቂ ቃሊቲ እና ኢትዮጵያ መድን አሰልጣኝ ሆነው ከሰሩ በኋላ ሻሸመኔን በተረከቡበት ዓመት ወደ ፕሪምየር ሊጉ የመለሱት አሰልጣኙ ጠንካራ ቡድን ለመገንባት ከአሁኑ ከከፍተኛ ሊግ እና ከፕሪምየር ሊጉ አዳዲስ ተጫዋቾችን ለማስፈረም በሒደት ላይ እንዳሉም ለማወቅ ተችሏል።
\"\"