የ2016 የዝውውር መስኮት የሚከፈትበት ቀን ታውቋል

በሁለቱም ፆታ በ2016 ለሚደረጉ የሊግ ውድድሮች የዝውውር መስኮቱ የሚከፈትበትን ቀን ፌዴሬሽኑ ይፋ አድርጓል።
\"\"
በ2016 በሁለቱም ፆታ ማለትም በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እና በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ላይ ተሳታፊ የሆኑ ክለቦች የተጫዋች ዝውውርን የሚፈፅሙበትን ቀን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ይፋ አድርጓል። በዚህም መሠረት የዝውውር መስኮቱ ከሐምሌ 8/2015 እስከ መስከረም 25/2016 ድረስ በሚቆይ ቀን ክለቦች ዝውውራቸውን እንዲፈፅሙ ቀነ ገደብን አስቀምጧል።
\"\"
ፌዴሬሽኑ አያይዞም የተጫዋቾች ዝውውር ህጋዊነቱ የሚረጋገጠው በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፅሕፈት ቤት ተገኝቶ በመፈራረም ብቻ መሆኑን ገልፆ በክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ጨምሮ በሌላ አካል በኩል የሚደረግ ስምምነት ተቀባይነት የሌለው መሆኑንም ጭምር ጠቁሟል።