ባህር ዳር ከተማ አንድ ተጫዋች ሲያስፈርም የአንድ ተጫዋች ውል አድሷል

በአሠልጣኝ ደግአረገ ይግዛው የሚመራው ባህር ዳር ከተማ ከከፍተኛ ሊግ የአንድ ተጫዋች ዝውውር ሲፈፅም የአንድ ነባር ተጫዋች ውልም አራዝሟል።
\"\"
በቀጣዩ ወር የካፍ ኮንፌዴሬሽን ካፕ የማጣሪያ ጨዋታ የሚጠብቀው ባህር ዳር ከተማ በዝውውሩ እየተሳተፈ የሚገኝ ሲሆን በዛሬው ዕለትም የግብ ጠባቂው ይገርማል መኳንንትን ውል ለተጨማሪ ዓመት ማራዘሙ ታውቋል።
\"\"
ከዚህ በተጨማሪ ክለቡ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ያሳለፈውን ረጀብ ሚፍታህን አስፈርሟል። የቀድሞ የኮልፌ ቀራኒዮ የቀኝ መስመር ተከላካይ ዓምና በቤንች ማጂ ቡና ያሳለፈ ሲሆን አሁን በውሀ ሰማያዊዎቹ ቤት የእግርኳስ ህይወቱን ለመቀጠል ፊርማውን አኑሯል።