ዳዋ ሆቴሳ ሀድያ ሆሳዕናን ለመቀላቀል ከስምምነት ደርሷል

ሀድያ ሆሳዕና የቀድሞው ተጫዋቹን ለማስፈረም ስምምነት ፈፅሟል።\"\"
በቀጣዩ ዓመት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ በአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ እየተመራ ወደ ውድድር እንደሚገባ የሚጠበቀው ሀድያ ሆሳዕና በርካታ ዝውውሮችን ከሰሞኑ እንደሚፈፅም የሚጠበቅ ሲሆን የመጀመሪያ ፈራሚው ከሁለት ዓመት በፊት በክለቡ ተጫዋቶ ያሳለፈውን ዳዊ ሆቴሳን ለማድረግ ክለቡ እና ተጫዋቹ በሁሉም ጥቅማጥቅሞች ጉዳይ ስምምነት ስለ መፈፀማቸው የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ አባተ ተስፋዬ ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
\"\"
እግር ኳስን በክለብ ደረጃ በናሽናል ሲሚንቶ ከጀመረ በኋላ በቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ አዳማ ከተማ እና ሀድያ ሆሳዕና መጫወት የቻለው አጥቂው ከሀድያ ጋር ተለያይቶ ወደ ቀድሞው ክለበ አዳማ ተመልሶ ሁለት የውድድር ዓመታት ካሳለፈ በኋላ ከዚህ ቀደም መጫወት ወደ ቻለበት ሀድያ ሆሳዕና ለመጫወት ስምሞነት ፈፅሟል። ተጫዋቹም ነገ አልያም ከነገ በስቲያ ፊርማውን እንደሚያኖር ይጠበቃል።