ሀምበሪቾ ዱራሜ የአሰልጣኙን ውል አራዝሟል

ሀምበሪቾ ዱራሜ ከከፍተኛ ሊጉ ያሳደጉትን አሰልጣኝ ውል በዛሬው ዕለት አድሷል።
\"\"
በ2015 የከፍተኛ ሊግ ተሳትፎውን በምድብ ሐ ስር ተደልድሎ ሲወዳደር ቆይቶ ምድቡን በበላይነት በማጠናቀቁ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በቀጣዩ ዓመት በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ተሳታፊ የሆነው ሀምበሪቾ ዱራሜ ለቀጣዩ የሊግ ጉዞው ዘግየት ብሎም ቢሆን ከታችኛው የሊግ ዕርከን ያሳደጉትን የአሰልጣኝ ደጉ ዱባሞን ውል ማራዘሙን ዝግጅት ክፍላችን የደረሰው መረጃ አመላክቷል።
\"\"
በመተሐራ ስኳር የአሰልጣኝነት ህይወትን የጀመሩት አሰልጣኝ ደጉ በመቀጠል በአዳማ ከተማ በረዳትነት እና በጊዜያዊ አሰልጣኝነት የሰሩ ሲሆን ሀምበሪቾ ዱራሜን በ2014 አጋማሽ ላይ ተረክበው ቡድኑ ሽንፈት ሳያስተናግድ ዘንድሮ ወደ ሊጉ እንዲያድግ ማድረጋቸው ይታወሳል።