ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ግብ ጠባቂ አስፈርሟል

አዳዲስ ተጫዋቾችን እያስፈረመ እንዲሁም የነባሮችን ውል እያደሰ የሚገኘው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዛሬው ዕለት የግብ ዘብ ማስፈረሙ ታውቋል።
\"\"
በ2016 ከአምስት ዓመታት በኋላ በሊጉ ተሳትፎ የሚያደረግው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስድስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የሁለት ነባር ተጫዋቾችን ውል ማራዘሙ ይታወቃል። አሁን ደግሞ ሰባተኛ ፈራሚ ተጫዋች በመሆን ግብ ጠባቂው ፍሬው ጌታሁን በሁለት ዓመት ውል ቡድኑን መቀላቀሉን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።
\"\"
ከአርሲ ነገሌ ወደ ፈረሰኞቹ ቤት በመቀላቀል ቆይታ ያደረገው ፍሬው በመቀጠል በአዲስ አበበ ከተማ ከተጫወተ በኋላ ያለፉትን ስድስት ዓመታት በድሬደዋ ከተማ ግልጋሎት ሲሰጥ እንደነበር አይዘነጋም።