ሀድያ ሆሳዕና ሁለት ተጫዋቾችን አስፈረመ

ከደቂቃዎች በፊት አንድ ተጫዋች ያስፈረሙት ሀድያ ሆሳዕናዎች በይፋ የሁለት ተጫዋቾችን ዝውውር በአሀኑ ሰዓት ቋጭቷል።

ከቀጣዩ የውድድር ዓመት ጀምሮ በአዲሱ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ መሪነት የሊግ ተሳትፎውን የሚጀምረው ሀድያ ሆሳዕና በዝውውር መስኮቱ የነቃ ተሳትፎን በማድረግ በረከት ወልደዮሐንስ እና ምህረተአብ ገብረህይወትን የግላቸው በማድረግ የነባር ተጫዋቾችን ውልም ያደሱ ሲሆን ከደቂቃዎች በፊት ደግሞ ቴዎድሮስ ታፈሰን አስፈርመዋል። አሁን ደግሞ የሁለት ተጫዋቾችን ዝውውር መቋጨታቸውን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።
\"\"
ዳዋ ሆቴሳ በይፋ ክለቡን ተቀላቅሏል። ከቀናቶች በፊት ከክለቡ ጋር ስምምነት የፈፀመው የቀድሞው የናሽናል ሲሜንት ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና አዳማ ከተማ ተጫዋች በይፋ ከሰዓታት በፊት ቀደም ብሎ ወደ ተስማማበት የቀድሞው ክለቡ ተመልሷል።
\"\"
የክለቡ አራተኛ ፈራሚ አይቮሪኮስታዊው የግብ ዘብ ታፔ ኤልዛየር ሆኗል። ለሀገሩ ብሔራዊ ቡድን በአሁኑ ሰዓት እያገለገለ የሚገኘው ቁመታሙ ግብ ጠባቂ ኤፍ ሲ ሳንፔድሮን ከለቀቀ በኋላ የተጠናቀቀውን የውድድር ዘመን ከባህርዳር ጋር አሳልፎ ቀጣዩ መዳረሻው ሀድያ ሆሳዕና ሆኗል።