ሀምበሪቾ ዱራሜ ወጣቱን የግራ መስመር ተከላካይ አስፈረመ

የቅዱስ ጊዮርጊሱ ረመዳን ዩሱፍ ታናሽ ወንድም የሀምበሪቾ ዱራሜ ሁለተኛው ፈራሚ ሆኗል።

\"\"

የሊጉ አዲሱ ተካታፊ ክለብ የሆነው ሀምበሪቾ ዱራሜ ለ2016 የፕሪምየር ሊጉ ጉዞው በትላንትናው ዕለት የኋላሸት ፍቃዱን የመጀመሪያው ፈራሚ ያደረገ ሲሆን የሁለት ነባር ተጫዋቾችን ውልም ማራዘሙ ይታወሳል። በዛሬው ዕለት ደግሞ ክለቡ ሁለተኛውን ፈራሚ ተጫዋች በማድረግ በቅዱስ ጊዮርጊስ የግራ መስመር የሚጫወተው ረመዳን የሱፍ ታናሽ ወንድም የሆነው አብዱሰላም የሱፍን ሁለተኛ ተጫዋቹ በማድረግ በይፋ አስፈርሟል።

በግራ መስመር ተከላካይነት በኮልፌ ቀራኒዮ ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የተጠናቀቀውን የውድድር ዘመን በደሴ ከተማ ጥሩ የውድድር ዓመትን በከፍተኛ ሊጉ ያሳለፈው ተጫዋቹ ክለቡን በይፋ በዛሬው ዕለት ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል።

\"\"