ንግድ ባንክ አማካይ አስፈረመ

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች በአንድ ዓመት ውል አስፈርሟል።
\"\"
በአዳማ ከተማ ከትናንት በስትያ ለ2016 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዝግጅታቸውን የጀመሩት ኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች በዝውውር መስኮቱ እስከ አሁን ወደ አስራ ሁለት የሚጠጉ አዳዲስ ተጫዋቾችን ያስፈረሙ ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ ከሰሞኑ በስምምነት ከኢትዮጵያ መድን ጋር የተለያየውን አማካይ ሀብታሙ ሸዋለምን በአንድ ዓመት ውል ክለቡ ማስፈረሙን ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ አመላክቷል።
\"\"
የቀድሞው የስሑል ሽረ ፣ አዳማ ከተማ እና ወልቂጤ ከተማ አማካይ የነበረው ሀብታሙ የተጠናቀቀውን የውድድር ዘመን ከኢትዮጵያ መድን ጋር ያሳለፈ ሲሆን ከሰሞኑ ቀሪ የአንድ ዓመት ውል ከቡድኑ ጋር እየቀረው ከተለያየ በኋላ ቀጣዩ መዳረሻው ንግድ ባንክ ሆኗል።