ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአሠልጣኙን ውል አራዝሟል

አሠልጣኝ ብርሀኑ ግዛው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ክለብ ለ14ኛ አመት የሚቆዩበትን ውል ተፈራረሙ።
\"\"
በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የሚሳተፈው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከፊቱ ላለበት አህጉራዊ ውድድር ዝግጅቱን በሀዋሳ ከተማ አከናውኖ ትናንት አመሻሽ ወደ መዲናችን አዲስ አበባ ገብቷል። ከቀናት በፊት ቡድኑ ሦስት አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሞ ውላቸው ያለቀባቸው ነባርችንም ውል ሲያድስ ከቆየ በኋላ በዛሬው ዕለት የአሠልጣኙ ብርሃኑ ግዛውን ውል ለተጨማሪ ዓመት አራዝሟል።
\"\"
24 ዓመታትን በአሠልጣኝነት ያሳለፉት አሠልጣኝ ብርሃኑ ግዛው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ከ2004 የውድድር ዓመት ጀምሮ እያሰለጠኑ እንደሚገኝ ይታወሳል። ከ2004 ጀምሮም ለክለቡ 6 የፕሪምየር ሊግ ዋንጫዎችን ጨምሮ አጠቃላይ አስራ ሦስት ዋንጫዎችን አስገኝተውለታል። በቀጣይ ሁለት ዓመታት ማለትም በኢትዮጵያ እግርኳስ ባልተለመደ ሁኔታ በክለቡ 14 ተከታታይ ዓመታት የሚቆዩበትን ውል በይፋ መፈራረማቸውን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።