ሀድያ ሆሳዕናዎች የቅድመ ውድድር ዝግጅት የሚጀምሩበት ቀን ታውቋል

በአዲሱ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ የሚመሩት ሀድያ ሆሳዕናዎች የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን የሚጀምሩት ቀን ይፋ ሆኗል።
\"\"
በ2016 የፕሪምየር ሊጉ ጉዞው አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌን ዋና አሰልጣኙ ካደረገ በኋላ በመቀጠል ዶ/ር እያሱ መርሀፅድቅን በረዳት ቦታ ላይ የሾመው ሀድያ ሆሳዕና ራሱን ለማጠናከር ምህረተአብ ገብረህይወት ፣ ዳዋ ሆቴሳ ፣ ቴዎድሮስ ታፈሰ ፣ በረከት ወልደዮሐንስ እና አይቮሪያኑን የግብ ዘብ ታፔ ኤልዛየርን አዳዲስ ፈራሚው አድርጎ ሲያስፈርም የተከላካዩ ዳግም በቀለን ውል ማደሱም ይታወሳል። በቀጣዮቹ ቀናትም የአዳዲስ ተጫዋቾችን ዝውውር ከሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ እንደሚፈፅም የሚጠበቀው ክለቡ የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን የሚጀምርበት ቀን ታውቋል።
\"\"
የፊታችን ዓርብ ነሀሴ 5 የክለቡ የልዑክ ቡድን መቀመጫ ከተማ ሆሳዕና ከተሰባሰቡ በኋላ በማግስቱ ቅዳሜ ነሀሴ 6 ዝግጅታቸውን በይፋ እንደሚጀምሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።