ቢንያም አሰፋ ወደ ኢትዮ ኤሌክትሪክ አምርቷል

ኢትዮ ኤሌክትሪክ አንጋፋው አጥቂ ቢንያም አሰፋን በአንድ አመት ኮንትራት አስፈርሟል፡፡

ቢንያም ባለፈው ክረምት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ለቆ ወደ ጅማ አባ ቡና ቢያመራም በጉዳት ጨዋታ ሳያደርግ ከግማሽ አመት በኋላ ወደ ቀድሞ ክለቡ ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመመለስ መልካም ጊዜ አሳልፏል፡፡ በክረምቱ ከኢብራሂማ ፎፋና እና ፍፁም ገብረማርያም ጋር የተለያየው ኤሌክትሪክ የአጥቂ መስመሩን ክፍተት ለመድፈን ኃይሌ እሸቱ፣ ጫላ ድሪባ እና ድድዬ ለብሪን ያስፈረመ ሲሆን አሁን ደግሞ ቢንያም አሰፋን በአጥቂ መስመሩ ላይ አክሏል፡፡

ቢንያም ከ1990ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ በወንጂ ስኳር፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ሰበታ ከተማ ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (በሶስት ጊዜያት)፣ ኢትዮጵያ ቡና እና ጅማ አባ ቡና የተጫወተ ሲሆን በ1998 የፕሪምየር ሊጉ ኮከብ ተጫዋች ተብሎ ተመርጧል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *