አዲስ ወርቁ ወደ አል ሂላል አምርቷል

የሱዳኑ ታላቅ ክለብ ኢትዮጵያዊው አሰልጣኝ ምክትል አሰልጣኙ አድርጎ መቅጠሩን አስታወቀ።


በትናንትናው ዕለት ከፈረሰኞቹ ጋር መለያየቱን በማሕበራዊ ትስስር ገፁ ይፋ ያደረገው አዲስ ወርቁ ወደ ሱዳኑ ታላቅ ክለብ አል አህሊ ማቅናቱ ተረጋግጧል። ከደቂቃዎች በፊት ክለቡ ይፋ ባደረገው መረጃ ኢትዮጵያዊው ምክትል አሰልጣኝ እና ፐርፎርማንስ አናሊስት ክለቡን መቀላቀሉን ገልፅዋል።

ላለፉት ስድስት ዓመታት ፈረሰኞቹን በተለያዩ የስራ መደቦች ማገልገል የቻለው ይህ ወጣት አሰልጣኝ በሱዳኑ ክለብ ቆይታው የፍሎረንት ኢቤንጌ ምክትል አሰልጣኝ ሆኖ የሚሰራ ይሆናል።

ከዚህ ቀደም አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የአህሊ ሸንዲ ምክትል አሰልጣኝ እና ዋና አሰልጣኝ ሆኖ መስራቱም ይታወሳል።