ኢትዮጵያ መድኖች ተከላካይ አስፈረሙ

በአሠልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ የሚመሩት ኢትዮጵያ መድኖች የቀድሞ ተጫዋቻቸውን አስፈርመዋል።

በአዳማ ከተማ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን በማድረግ ላይ የሚገኙት ኢትዮጵያ መድኖች የቀድሞ ተከላካያቸው መልሰው አስፈርመዋል። ባለፈው የውድድር ዓመት ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ያሳለፈው ማታይ ሎይ ወደ ቀድሞ ክለቡ የተመለሰ ተጫዋች ነው። ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ መድን እና አዲስ አበባ ከተማ መጫወት የቻለው ይህ ተጫዋች ከክለቡ ጋር የቅድመ ውድድር ዝግጅት እያከናወነ እንደሚገኝም ሰምተናል።

በርካታ ወሳኝ ተጫዋቾቻቸውን ያጡት ኢትዮጵያ መድኖች ተጨማሪ ዝውውሮች ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።