ሲዳማ ቡና ጋናዊ የመስመር አጥቂ አስፈርሟል

የአሰልጣኝ ሥዩም ከበደው ሲዳማ ቡና ጋናዊ የመስመር አጥቂ አስፈርሟል።

የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን በሀዋሳ ከጀመሩ ሰንበትበት ያሉት ሲዳማ ቡናዎች እስከ አሁን የሀገር ውስጥ ተጫዋቾችን ሲያስፈርሙ የነበረ ሲሆን አሁን ደግሞ ፊታቸውንም ወደ ውጪው በማዞር የጋና ዜግነት ያለውን የመስመር አጥቂ ሚካኤል ኬፕሮቪን የግላቸው ስለ ማድረጋቸው ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ጠቁሟል።

ተጫዋቹ በአፍሪካ አህጉር ደረጃ ለሀገሩ ክለቦች ሶንዲሶ እና ኢንተር አላይንስ በመቀጠልም በሴኔጋሉ ኤ ኤስ ሲ ጂርፍ ፣ በሱዳኑ ኤልሜሪክ ፣ በአይቮሪኮስቱ አፍሪካን ስፖርትስ ግልጋሎት መስጠት የቻለ ሲሆን ወደ ህንድ በማምራትም ያለፉትን አራት ዓመታት በቢ ኤስ ኤስ እና በኔሮካ ከተጫወተ በኋላ ወደ ሀገራችን በመምጣት ሲዳማ ቡናን ተቀላቅሏል።